ጀነራል ተፈራ ማሞ እስካሁን የት እንዳሉ ማወቅ አለመቻላቸውን ባለቤታቸውና የግል ጠባቂያቸው ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

ጀነራል ተፈራ ማሞ እስካሁን የት እንዳሉ ማወቅ አለመቻላቸውን ባለቤታቸውና የግል ጠባቂያቸው ተናገሩ

የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ጀነራል ተፈራ ማሞ ትናንት እረፋዱ ላይ ሰው ለማግኘት አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መውጣታቸውን የሚናገሩት ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይለማሪያም፤ ከቀኑ 10 ሰዓት በኋላ በእጅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ቢደውሉም እንደማይነሳና ዛሬም ወደ ተለያዩ የፍትህ ተቋማት ቢሄዱም ምላሽ አለማግኘታቸውን ተናግረዋል።

"ትናንት ረፋዱ ላይ ከአቶ ዩሐንስ ቧያለው ጋር ቀጠሮ እንዳለውና እርሱን ለማግኘት እንደሚሄድ ነግሮኝ ነበር ከቤት የወጣው” ያሉት ወ/ሮ መነን “ሁሌ ስብሰባ ወይም ሌላ ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስድ ጉዳይ ሲኖረው ስልክ ደውሎ ወይም በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ያለበትን ሁኔታ ያሳውቅ ነበት ትናንት ግን ይህን አላደረገም። ሁኔታው አላምር ሲለኝ ስልኬን አንስቼ ደጋግሜ ደወልኩ ስልኩ አይነሳም አቶ ዩሀንስ ጋር ደወልኩ እስከ 10:30 ድረስ አብረው እንደነበሩና ወደ መኪናው አስገብቶት እንደተለያዩ ነገረኝ ማታም የቅርብ ዘመዶቻችን ጋር ስደዋውል አየሁት የሚል ሰው አላገኘሁም" ብለዋል።

ዛሬ ጠዋት ፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቢሄዱም ሊያገኟቸው እንዳልቻሉና በኋላም ወደ ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ ሲሄዱ በነገው ዕለት ወረቀት ጽፈው ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ እንደተነገራቸው ገልፀዋል።

ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ