የደራሼ ግጭት በመባባሱ መንገድ መዘጋቱን ነዋሪዎች እና አሽከርካሪዎች ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

የደራሼ ግጭት በመባባሱ መንገድ መዘጋቱን ነዋሪዎች እና አሽከርካሪዎች ገለፁ

በደቡብ ክልል ደራሼ ልዩ ወረዳ እና አከባቢው የተፈጠረው የፀጥታ ችግር በመባባሱ መንገድ መዘጋቱና የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎሉን የአሜሪካ ድምፅ በስልክ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እና መንገደኞች ተናገሩ።

የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በግጭት ውስጥ የተሳተፉትን እና ያልተሳተፉትን ባልለየ መልኩ ሰዎችን በጅማ ማፈስ ስለጀመሩ ነዋሪው ሸሽቶ ወደ ጫካ እየገባ መሆኑን ነዋሪዎቹ ጨምረው ገልፀዋል።

በመንግሥት ላይ የሚቀረበውን ወቀሳ በተመለከተ ከክልሉ መንግሥትም ሆነ ከጊዜያዊ ወታደራዊ ዕዝ በኩል የተሰጠ አስተያየትም ሆነ የወጣ መግለጫ የለም።

ዘገባውን ያሰናዳው ዮናታን ዘብዲዮስ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።