አፋር እና አማራን ክልል በሚያጎራብት ቦታ ታጣቂዎች አደረሱት በተባለ ጥቃት ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

አፋር እና አማራን ክልል በሚያጎራብት ቦታ ታጣቂዎች አደረሱት በተባለ ጥቃት ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ

በአፋር ክልል ዞን አንድና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አጎራባች አካባቢዎች የሚከሰተውን የጸጥታ ችግር በመቅረፍ እና በችግሩ ምክንያት የተዘረፉ ንብረቶችን በማስመለስ ሂደት ላይ በነበሩ የሁለቱም ወገን አመራሮች ላይ ለጊዜው ማንንታቸው አልታወቀም የተባሉ ታጣቂዎች በሰነዘሩት ጥቃት ከአራት የማያንሱ ሰዎች መሞታቸውን እና ወደ ዐስር የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ተገለጸ፡፡

ከኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ወሰንተኛ የሆነው የአፋር ክልሉ አድአር ወረዳ ድርጊቱ ሁለቱንም ወገኖች ለማጥፋት ሆን ተብሎ የታቀደ ነበር ሲል አስታውቋል፡፡

ድርጊቱን የፈጸሙት አካላት ለጊዜው ማምለጣቸው ተሰምቷል፡፡

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳዳር ዞን ጥቃቱ ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ እለት የተፈጸመ ሲሆን ግጭቱ የብሔር መልክ እንዳይዝ በተደረገው ጥንቃቄ አሁን አካባቢዎቹ በአንጻራዊ ሰላም ይገኛሉ ነው ብሏል።

ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ