ጽንስ ማቋረጥን የሚደግፉ ቡድኖች በመላው ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ ሰልፍ ይወጣሉ

ሮቪ ዌ ድ የተሰኘው ጽንስ ማቋረጥ ደጋፊዎች

ጽንስ ማቋረጥን የሚደግፉ አክቲቪስቶች ዛሬ ቅዳሜ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ ‘የበጋው ቁጣ’ የተሰኘ ሰልፍ ጠርተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሮ ቪ ዌድ በተሰኘው እና የጽንስ ማቋረጥን በመላው ሃገሪቱ የሚፈቅደውን ሕግ የሚቀልብስ ከሆነ በእቅድ የሚመራ ቤተሰብ የተሰኘ ተቋምን ጨምሮ ሌሎች ጽንስ ማቋረጥን የሚደግፉ ተቋማት እና ቡድኖች በመላው ሃገሪቱ ከ300 በላይ በሚሆኑ ከተሞች “ከሰውነታችን ራቁ” የተሰኙ ሰልፎችን አዘጋጅተዋል። በዋሺንግተን ዲሲ ፣ኒው ዮርክ፣ ሎስ አንጀለስ እና ቺካጎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በሰልፉ ላይ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል ስቱደንትስ ፎር ላይፍ ኦፍ አሜሪካ የተሰኙ ጽንስ ማቋረጥ የሚቃወሙ ቡድኖችም በተመሳሳይ ዋሺንግተን ዲሲን ጨምሮ በዘጠኝ ከተሞች ላይ ሰልፍ እናካሂዳለን ሲሉ አስታውቀዋል።