የትግራይ ክልል ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ የማይፈታ ከሆነ ወደ ጦርነት ሊገባ እንደሚችል ክልሉ አስታወቀ

ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ

ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ

የትግራይ ክልል አመራሮች በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች ከሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ሰሞኑ ባደረጉት ውይይት፤ ነገሮች በሰላማዊ መንገድ የማይፈቱ ከሆነ ሕዝቡ ሳይወድ በግድ ሕልውናውን እና ዋስትናውን ለማረጋገጥ ወደ ጦርነት እንደሚገባ መግባባት ላይ መደረሱን የክልሉ መንግሥት ገለፀ።

በሕዝባዊ ውይይቱ ላይ የተሳተፉ አንድ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ በሰጡት አስተያየት፤

“የክልሉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሕዝቡን ሕልውና ለማረጋገጥ መጀመሪያ የምንወስደው እርምጃ ሰላማዊ ድርድር ባሉበት ጊዜ ሕዝቡ በትልቅ ጭብጨባና እልልታ ተቀብሎታል።” ሲሉ እርሳቸው በተሰበሰቡበት አዳራሽ ያለሁን ሁኔታ ተናግረዋል። አያይዘውም፣

“እንዲህም ተቀብሎ ይህ አማራጭ ከታጣ ግን ወደ ጦርነት እንደሚገባ ሲነገረም በተመሳሳይ ተቀብሎታል ይሄ ሕዝብ” ብለዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት ከትግራይ ክልል ጋር የገባበትን ጦርነት በሰላም ለመፍታት “እያደረኩት ነው” ያለውን ጥረት በህወሓት አመራሮች ተቀባይነት እንዳላገኘ እና በአንፃሩም ህወሓት አማራና አፋር ክልል ውስጥ ትንኮሳ እየፈፀመ መሆኑን በትናንትናው ዕለት መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሰደር ዲና ሙፍቲ መናገራቸው አይዘነጋም።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ::

Your browser doesn’t support HTML5

የትግራይ ክልል ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ የማይፈታ ከሆነ ወደ ጦርነት ሊገባ እንደሚችል ክልሉ አስታወቀ