የደቡብ ኦሞ ዞን አሪ ወረዳ ተፈናቃዮች ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

የደቡብ ኦሞ ዞን አሪ ወረዳ ተፈናቃዮች ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ

ቤታቸው ተቃጥሎ፣ ንብረታቸው ወድሞ ሜዳ ላይ ከተጣሉ በኋላ የጠየቃቸው አካል እንደሌለ ከደቡብ ክልል አሪ ዞን ወረዳ የተፈናቀሉ ዜጎች ምሬታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ባንቄ ኩሜ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም 72 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። እስከ ሰኔ ድረስ ወደ ቀያቸው ለመመለስም ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተናግረዋል።

የዞኑ ሰላምና የፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ በዛብህ ዴሞ በኩላቸው በወንጀሉ የተጠረጠሩ ከ1400 በላይ ሰዎች መያዛቸውን እና የማጣራት ሥራ ተሠርቶ በወንጀሉ ዋና ተዋናይ በሆኑና ማስረጃ በሚገኝባቸው ክስ ለመክፈት በሂደት ላይ እንደሚገኙ ገልጠዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ።