በደራሼና ኮንሶ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ አካባቢው ላይ ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ

Your browser doesn’t support HTML5

በደራሼና ኮንሶ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ አካባቢው ላይ ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ

በደቡብ ክልል ደራሼ ልዩ ወረዳ በጊዜያዊ ወታደራዊ ዕዝ ሥር እንዲተዳደር ተወስኖ ተወስኖ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አከባቢውን መረከቡንና መቆጣጠሩን ክልሉ አስታወቀ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ እና የክልሉ የሰላም እና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ፤ መንግሥታዊ መዋቅሩን አፍርሶ የራሱን ሕገ ወጥ ሥርዓት ለመዘርጋት አቅደው ነበር የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

ባለፈው ቅዳሜ የወረዳውን አስተዳዳሪ ጨምሮ ሌሎች የአካባቢው ባለሥልጣናትን፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የክልሉ ልዩ ኃይል አባላትን ገደለ የተባለው ቡድን አምስት መሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ተናግረዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።