“የአማራ ድምፅ” አዘጋጅ መታሰሩን እና የት እንዳለ እንደማያውቁ ቤተሰቦቹ ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

- የኦሮምያ ኒውስ ሚዲያ ዘጋቢዎች እንዲፈቱ ሲፒጄ ጠየቀ

ከትናንት በስቲያ መደበኛ ልብስ በለበሱ ታጣቂዎች ከመኖሪያ ቤት የተወሰደው የአማራ ድምፅ የተሰኘው የኢንተርኔት ላይ ሚዲያ አዘጋጅ ጎበዜ ሲሳይ “የትና በምን ሁኔታ እንዳለ ማወቅ አልቻልንም” ሲሉ የግል ጠበቃውና ቤተሰቦቹ ገልፀዋል።

ጠበቃ አዲሱ አልጋው ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ወደ ሚመለከታቸው የፍትህ ተቋማት ተዘዋውረው መጠየቃቸውንና ምንም ዓይነት መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉ ገልፀዋል።

የአማራ ድምፅ የተሰኘው የድጅታል ሚድያ አዘጋጅ ጎበዜ ሲሳይ ባለፈው እሁድ ሲቪል በለበሱ የመንግሥት ታጣቂዎች ከመኖሪያ ቤቱ እንደተወሰደ እና አሁን የትና በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ማወቅ አለመቻላቸውን የአዘጋጁ የግል ጠበቃ አዲሱ አልጋው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በእስር ላይ ሚገኙትና ሁለቱ የኦሮሚያ ኒውስ ሚዲያ ዘጋቢዎች ደሱ ዱላ እና ቢቂላ አመኑክሳቸው ውድቅ ተደርጎ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት ሲፒጄ ጠይቋል።

በጉዳዩ ላይ የሁሉንም ተከሳሽ ጠበቆች አነጋግረናል ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።