የተመድ ዋና ጸሃፊ ኒጀር ገቡ

ፎቶ ፋይል - የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ኦዋላም ኒጀር በሚገኘው የተፈናቃዮች ካምፕ እአአ ግንቦት 3 ቀን 2022

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ በሦስት የምዕራብ አፍሪካ አገሮች የሚያደርጉትን ጉብኝት በመቀጠል ትናንት ረፋዱ ላይ ኒጀር ገብተዋል፡፡

ዋና ጸሃፊው በኒጀር ከፕሬዚዳንት መሃመድ ባዙም ጋር የተነጋገሩ ሲሆን በአገሪቱ የተንሰራፋው ሽብርተኝነት ለመዋጋት ተጨማሪ የዓለም አቀፍ ድጋፍ ጠይቀዋል፡፡

ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ባላፈው እሁድ ከሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ጋር፣ በዳካር ተገናኝተው ተነጋግረዋል፡፡

በወቅቱም ባደረጉት ጥሪ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በተካሄደባቸው፣ በቡርኪና ፋሶ፣ ጊኒና ማሊ የሚገኙ አምባገነን መሪዎች ሥልጣንን ለሲቪሎች በአስቸኳይ እንዲያስረክቡ ማሳሳባቸው ይታወሳል፡፡