ምዕራባውያን ሩሲያ በቡድን 20 ስብሰባ እንዳትሳተፍ ግፊት እያደረጉ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

ፋይል- እ.አ.አ በጥቅምት 30 2021 ዓ.ም በሮም በተካሄደው የቡድን 20 ሀገራት ስብሰባ የተሳተፉ የዓለም መሪዎች 

ቀጣዩን የቡድን 20 ስብሰባ የምታስተናግደው ኢንዶኔዥያ ፕሬዝዳንት ጆኮ ዊዶዶ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቩለድሚር ዚለንስኪ እንዲገኙ ጥሪ አቅርበውላቸዋል። ሆኖም የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑትን ስብሰባውን ለመታደም ማቀዳቸውን መግለፃቸውን ተከትሎ የዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች ምዕራብ ሀገራት በስብሰባው መገኘታቸው አጠራጣሪ ሆኗል።

በኢንዶኔዥያ ዋና ከተማ በባሊ የሚካሄደው የዘንድሮ ቡድን 20 ስብሰባ "አብረን እናገግም፣ ስናገግም እንጠንክር" በሚል መሪህ ቃል የሚደረግ ቢሆንም የኢንዶኔዥያ ፕሬዝዳንት ጆኮ ዊዶዶ ሩሲያን ከስብሰባው ተሳታፊዎች ዝርዝር እንዲሰርዙ ከምዕራብ ሀገራት ከፍተኛ ግፊት እየተደረገባቸው ነው።

የዋይት ኃይት ፕሬስ ፀሃፊ ጂን ሳኪ ሩሲያ ለስብሰባው ጥሪ የተላለፈላት ከስብሰባው በፊት ቢሆንም አሁን ግን መገኘት እንደሌለባቸው ለኢንዶኔዥያ አሳውቀናታል ብልዋል። ሆኖም ቻይና ሞስኮ በስብሰባው እንድትሳተፍ መደገፏ ዊዶዶን አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተታቸው ተዘግቧል።