የሰብዓዊ ድርጅቶች ያለምንም ገደብ ወደ ትግራይ ክልል እንዲንቀሳቀሱ መፈቀዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የሰብዓዊ ድርጅቶች ያለምንም ገደብ ወደ ትግራይ ክልል እንዲንቀሳቀሱ መፈቀዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ከግጭት ማቆም ውሳኔው በኋላ 146 የሰብዓዊ ድጋፎችን የጫኑ ተሸከርካሪዎች ትግራይ ክልል መግባታቸውን መንግሥት አስታወቀ። ይሁን እንጂ ወደክልሉ የሚገባው የሰብዓዊ ድጋፍ እጅግ አነስተኛ መሆኑን የትግራይ ክልል አመራሮች በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ታዲያ፣ የሰብዓዊ ድርጅቶች ያለምንም ገደብ ወደትግራይ ክልል እንዲንቀሳቀሱ መፈቀዱን ገልጸው፣ ከአቅርቦት አንጻር ግን እጥረት እንዳለተናግረዋል፡፡

ለዕርዳታ አቅርቦቱ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በሚል ህወሓት በአፋር ክልል ከያዛቸው አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ለቆመውጣቱን ቢገልጽም፣ ይህ ሐሰት መሆኑን ያመለከቱት አምባሳደር ዲና ይልቁንም ህወሓት ጥቃት የመክፈት ፍላጎት አለው ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ያዳምጡ።