በጎንደሩ ግጭት የበርካታ ሰው ህይወት ጠፋ

ጎንደር ከተማ

ትናንት በጎንደር ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት በሰዎች ህይወት፣ አካል ጉዳትና ንብረት ውድመት ምክንያት የሆኑ አካላት ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ፡፡

በግጭቱ የሞቱና የተገዱ ሰዎችን አጣርቶ ይፋ እንደሚደርግም የክልሉ መንግሥት ትናንት ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር በበኩሉ በግጭቱ የእስልምና እና የክርስትና ዕምነት ተከታይ የሆኑ የከተማይቱ ነዋሪዎች መገደላቸውን አመልክቷል፡፡

በሌላ በኩል በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ቤተ እምነቶች ባስተላላፉት ጥሪ "መንግሥት ለንጹሃን ሞት ምክንያት የሆኑ ህገ ወጥ ተግባራትን ያስቁም" ብለዋል። "'.. ማንም ይሁኑ ማን ድርጊቱን የፈጸሙ ወገኖችንም ተጠያቂ እንዲያደርግ” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በጎንደሩ ግጭት የበርካታ ሰው ህይወት ጠፋ