የእርዳታ እህል እና ነዳጅ የጫኑ ተሸከርካሪዎች መቀሌ መግባታቸው ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

የእርዳታ እህል እና ነዳጅ የጫኑ ተሸከርካሪዎች መቀሌ መግባታቸው ተገለጸ

ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 15 ከአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የተነሱ 74 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በአባአላ መንገድ በኩል ወደ ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ መድረሳቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለቪኦኤ አረጋግጠዋል፡፡

የትግራይ ክልልን በመምራት ላይ የሚገኙት ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤል ለተባበሩት መንግስታት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ጻፉት በተባለ ግልጽ ደብዳቤ፣ የፌዴራሉ መንግስት የእርዳታ መተላለፊያ መስመሮችን ደህንነት ሊያስጠብቁ እንደሚገባ ያመለከቱ ሲሆን፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በበኩላቸው የእርዳታ መስመሮቹ የደኅንነት ሥጋት የህወሓት ታጣቂዎች ናቸው ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።