የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት ለባይደን ደብዳቤ ፃፈ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ለባይደን ደብዳቤ ፃፈ

ኤችአር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ህጎችን የተቃወመው የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ለፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ግልጽ ደብዳቤ ፅፏል።

በሥሩ 3700 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ማቀፉን የሚገልፀው ይህ ምክር ቤት ሁለቱ ረቂቅ ህጎች ዩናይትድ ስቴትስ በውጭ ፖሊሲዋ ከምትከተለው የልማት፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ እሴቶች ጋር የሚቃረኑ ናቸው” ሲል በደብዳቤው ገልጿል።

“ረቂቆቹ የታሰቡለትን ዓላማ ከማሳካት ይልቅ ኢትዮጵያን ለባሰ ቀውስ የሚዳርጉ ናቸው” ሲሉ የምክር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ሄኖክ መለሰ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት እና ደጋፊዎቹ ሲቃወሙት፣ በህወሓት እና በደጋፊዎቹ ተቀባይነት ያገኙት እነዚህ ረቂቅ ሕጎች፣ ለሴኔቱ ሙሉ ድምፅ ከመቅረባቸው በፊት ሂደቱ እንዲዘገይ መደረጉ ቀደም ሲል ተዘግቧል።