ችግሮችን በሰላም ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

ችግሮችን በሰላም ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ

የኢትዮጵያን ችግሮች በሰላም ለመፍታት መንግሥት ዝግጁ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ባለፈው ሣምንት ከአፍሪካ ሕብረት የፖለቲካ፣ የሰላም እና የፀጥታ ጉዳዮች ኮሚሽነር፤ ባንኮሌ አዴኦዬ ጋር ተገናኝተው በዚሁ የሰላም ጉዳይ መወያየታቸውን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ድርቅና ግጭቶች ባሳደሩት ጫና ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ ከ24 ሚሊዮን በላይ ሰው ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።

“ከኢድ እስከ ኢድ” በሚል ስያሜ የቀረበውን ጥሪ በመቀበል ውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ወደ ሃገራቸው መግባት መጀመራቸውን አምባሳደር ዲና አመልክተዋል።

ለሩሲያ በውትድርና ለመመዝገብ ኢትዮጵያውያን ሩሲያ ኤምባሲ አጠገብ ተሰልፈው መታየታቸውን በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዘገባው የኬኔዲ አባተ ነው።