አማራ ክልል ውስጥ በጦርነት የተጎዱ ማኅበራዊ ተቋማት እንደገና ሊሠሩ ነው

የግንባታ ሥራ

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጉዳት በደረሰባቸው የምሥራቅ አማራ ሰባት ከተሞች ውስጥ የሚገኙ 18 ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ከዓለም ባንክና ከኢትዮጵያ መንግሥት በተገኘ የ150 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ መልሶ የመግንባት ሥራ መጀመሩን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ አስታውቀዋል።

ሥራውን በበላይነት የሚያስተባብረው ፌዴራሉ የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮጀክት የመልሶ ግንባታዎቹ ሥራዎች በአራት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቁ አመልክቷል።

መስፍን አራጌ ከከሚሴ ዘግቧል።

Your browser doesn’t support HTML5

አማራ ክልል ውስጥ በጦርነት የተጎዱ ማኅበራዊ ተቋማት እንደገና ሊሠሩ ነው