የምዕራብ አፍሪካ ውጥረትና አዳዲስ ሥጋቶች

Your browser doesn’t support HTML5

የምዕራብ አፍሪካ ውጥረትና አዳዲስ ሥጋቶች

ምዕራብ አፍሪካ ውስጥ አይቮሪ ኮስት ከቡርኪና ፋሶ ጋር ያላትን ድንበር እያጠናከረች ባለችበት ወቅት “እሥላማዊ ተዋጊዎችን ትደግፋላችሁ” በሚል በፀጥታ ኃይሎች እየተሳደዱ መሆናቸውን የፉላን ጎሣ አባላት አስታውቀዋል።

በኅብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደር አሉታዊ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችልና አድራጎቱ አማፂያኑ ተዋጊዎችን እንዲመለምሉ አመቺ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው የመብቶች ተሟጋች ድርጅቶች አስጠንቅቀዋል።

ሄነሪ ዊልክንስ ከአይቮሪ ኮስቷ ኮንግ ከተማ ያጠናቀረውን ዘገባ፣ ስመኝሽ የቆየ ታቀርበዋለች።