ወደ ትግራይ ክልል ዳግም ድጋፍ ማድረስ መጀመሩን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ

.

የህክምና አጋዥ ቁሳቁሶችን፣ ምግብ እና ውሃ አካሚ ግብዓቶችን የጫኑ መኪኖች በአፋር ክልል በኩል ከቅዳሜ ዕለት ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል እየገቡ እንደሆነ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ይፋ አደረገ ። መስከረም ወር ወዲህ ፣ በየብስ ትራንስፖርት መሰል ድጋፍ ወደ ክልሉ ሲደርስ የመጀመሪያው መሆኑ ድርጅቱ ባሰራጨው ጋዜጣዊ መግለጫ አመላክቷል ።

በርካታ በትግራይ ክልል የሚኖሩ ህዝቦች የጤና አገልግሎት፣ በቂ የምግብ አቅርቦት እና መሰረታዊ ቁሳቁሶች እና አገልግሎቶችን በማግኘት ረገድ በእጅጉ ፈታኝ በሆነ ሁኔታ እንደሚገኙ ያስታወሱት የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ልዑካን መሪ ኒኮላስ ቫን ፣ በቅርቡ የተደረሰውን የተኩስ አቁም እና በእጅጉ የሚያስፈልጉ ሰብዓዊ ድጋፎች ወደ ትግራይ እንዲገቡ መተላለፊያ ለመፍቅድ ሁለቱ ወገኖች ያሳዩትን ፍላጎት ተቋማቸው በበጎ እንደሚቀበለው አክለዋል ።አሁን ላይ በየብስ መጓጓዣ ወደ ክልሉ ከገባው ድጋፍ በተጨማሪ ተቋሙ ከጥር ወር ጀምሮ ኢንሱሊንን ፣ ሄሞ ዲያሊስስ፣ ኦክሲቶሲን፣ ቴታነስ ቶክሲድ የተባሉ መድሃኒቶችን ፣ የቀዶ ህክምና ቁሳቁሶችን እና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ያያዙ 40 ጭነቶችን በአየር ማጓጓዙን አስታውቋል ።

ይህ በእንዲህ እያለ፣ በአፋር ክልልል 9ሺ ያህል የግዛት ውስጥ ተፈናቃዮች፣ የስንዴ ዱቄት፣ አተር ክክ፣ጨውና ዘይትን የመሰሉ የምግብ ድጋፎች እንደተደረገላቸው ፣ ተጨማሪ፣9ሺ ሰዎች ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል ።