ከዓለም ሕዝብ አንድ ሦስተኛው በግጭት ውስጥ እየኖረ መሆኑ ተገለጸ

ፎቶ ፋይል፦ የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ኃላፊ ከዓለም ሕዝብ አንድ ሦስተኛው ወይም 2ቢሊየን የሚሆነው በግጭት አካባቢዎች እየኖረ ነው ያሉ ሲሆን ይሄ አሃዝም እአአ በ1945 ከነበረው የላቀ ነው ብለዋል።

ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ በየመን፣ በሶሪያ፣ ማይናማር፣ ሱዳን ሃይቲ እና በአፍሪካ ሳህል ክልል እንዲሁም በዩክሬን እየተካሄዱ ያሉ ግጭቶችን ያነሱ ሲሆን እነዚህ ግጭቶች ዓለም አቀፍ ሥርዓትን በመናጥ የምግብ፣ የነዳጅ እና የማዳበሪያ ዋጋዎችን በማናር ቀውሱን አባብሰውታል ብለዋል።

ጉቴሬዥ በትናንትናው ዕለት ከመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታ ኮሚሽን ጋር በነበራቸው ውይይት በዓለም ዙሪያ 84 ሚሊየን ሰዎች በግጭት ምክንያት ለሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመጋለጥ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል ብለዋል።

ይሄ አሃዝ ታዲያ ከዩክሬን የተፈናቀሉ 4 ሚሊየን ሰዎችን እና በዛው ያሉ 6.5 ሚሊዮኖችን ሳይጨምር መሆኑንም የመንግሥታቱ ድርጅት ተቋማት አስታውቀዋል።