የኢትዮጵያ መንግሥት የተናጥል የተኩስ ማቆም ማድረጉን አስታወቀ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ መንግሥት የተናጥል የተኩስ ማቆም ማድረጉን አስታወቀ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ አስቸኳይ የሰብዓዊ አቅርቦቶች ወደ ትግራይ ክልል በበቂ ሁኔታ መድረስ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማሳካት መንግሥት የተቻለውን ሁሉ ጥረቶች ለማድረግ ቁርጠኛ ነው ብሏል። ለሰብዓዊነት ሲባል የተላለፈው ግጭት የማቆም ውሳኔ፣ ይህ መግለጫ ከወጣበት ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግም ተጠቅሷል።

የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ፣ ውሳኔው የተላለፈው ለሰብዓዊ በረራዎች ደህንነት እና የህወሓት ታጣቂዎች በሥጋት እርዳታ የሚተላለፍበትን መንገድ እንዳይዘጉ ለማድረግ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ከሕወሓት በኩል በይፋ የተባለ ነገር የለም፡፡

በሌላ በኩል የትግራይ ክልል የውጭ ግንኙነት የሚባል ቢሮ አስተባባሪ መሆናቸውን የሚናገሩትና በካናዳ የሚገኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት አቶ ዩሃንስ አብርሃ ትናንት ከአሜሪካ ድምጽ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሰብዓዊ እርዳታን ተደራሽ ለማድረግ የተኩስ አቁም ሥምምነትን በተመልከተ ንግግሮች ቢደረጉም እስካሁን ድረስ ግን በተጨባጭ የተወሰነ ነገር አለመኖሩ መናገራቸው ይታወሳል፡፡