የቤንሻንጉል ክልል መንግሥትና የጉህዴን አመራሮች ታረቁ

Your browser doesn’t support HTML5

የቤንሻንጉል ክልል መንግሥትና የጉህዴን አመራሮች ታረቁ

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የክልሉ መንግሥትና መንግሥትና የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጉህዴን አመራሮች መካከል ሥምምነት መፈጠሩን አስታወቁ።

የክልሉ ኮሙኒኬሽንስ ጽሕፈት ቤት በመንግሥትና ጉህዴን መካከል ከትናንት በስቲያ በካማሺ ዞን እርቀ ሰላም መደረጉን አስታውቋል። በመተከል ዞንም እርቀሰላም ተካሂዶ ሰላምን የማስፈን ሥራ እንደሚሠራ ገልፀዋል።

የጉህዴን ሊቀ መንበር አቶ ግራኝ ጉደታ የእርሳቸውና የፓርቲያቸው አመራሮችና አባላት ከእስር መፈታት ለእርቀ ሰላሙ እንደ አንድ ቅደመ ሁኔታ ተቀምጦ የነበረ መሆኑን ጠቅሰው በመንግሥትና ታጣቂዎች መካከል የሚደረጉ ግጭቶች ሕዝቡን የሚጎዱ በመሆናቸው እርቀ ሰላም መፈጸሙ ሰላም ለማምጣት ተገቢ እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል። እርቀ ሰላሙ መፈጸሙ ያስደሰታቸው የአካባቢው ነዋሪዎችም አስተያየት ሰጥተዋል።