በዩክሬን የነበሩ አፍሪካዊያን ተማሪዎች ጭንቀት

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

በዩክሬን የነበሩ አፍሪካዊያን ተማሪዎች ጭንቀት

ሩሲያ ዩክሬንን መውረር እንደጀመረች ሸሽተው በሰላም ሊወጡ የቻሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ የናይጄሪያ ተማሪዎች የመመረቂያቸው ጊዜ ደርሶ ነበር። በጦርነት መካከል እንኳ ቢሆኑም፣ አንዳንድ የዩክሬን መምሕራን ተማሪዎቻቸውን በድረ ገጽ ላይ ማስተማሩን ቀጥለውበታል።

የደቡብ አፍሪካ የሕክምና ተማሪዎች የተቋረጠውን ትምሕርታቸውን የሚያጠናቅቁበትን መንገድ እየፈለጉ ነው። በሌላም በኩል የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ለተማሪዎቹ ያለውን አማራጭ እየተመለከቱ ነው። አንዳንዶቹ ተማሪዎች አሁንም ዩክሬን ውስጥ ያዩት ጥቃት ካሳደረሰባቸው ጭንቀት ገና አልወጡም ወደ ኋላ ትተዋቸው የወጡት መምሕራኖቻቸውና ጓደኞቻቸውም አሁንም ያሳስቧቸዋል፡፡

በቪኦኤ ሪፖርተሮች ከናይጄሪያ ቲሞቲ ኦቢዙ እና ከደቡብ አፍሪካ ቪኪ ስትራክ የተጠናቀሩትን ዘገባዎች ደረጀ ደስታ አቀናብሮታል።