ሰላማዊ ሰዎችን የገደሉና ያቃጠሉ ማንነታቸው ተለይቶ ተጠያቂ እንዲሆኑ ኢሰመኮ ጠየቀ

  • ቪኦኤ ዜና

አቶ ይበቃል ግዛው

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተጠርጣሪዎችን ከዳኝነት ውጪ መግደላቸውንና አስክሬናቸውን ማቃጠላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ማረጋገጡን አስታወቀ።

ለዚህ ድርጊት መንስኤ የሆነው ታጥቂዎች በመንግሥት ኃይሎችና ሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈፀሙትን ግድያም ማረጋገጡን ገልጿል። የኮሚሽኑ የክትትልና የምርመራ ክፍል ዳይሬክተር አቶ ይበቃል ግዛው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ፤ ከፀጥታ ኃይሎች በተጨማሪ ሲቪሎች በድርጊቱ ተሳታፊ እንደነበሩ በቪዲዮው ላይ መታየቱን ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ድርጊቱ እንዳስደነገጠው አስታውቆ ጉዳዩ ተጣርቶ ለሕግ እንዲቀርብ አሳስቧል።

በውጭ ሀገሮች “በትግራይ ክልል መንግሥት ስም” እንደሚንቀሳቀስ የሚናገረው ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ዮሃንስ አብርሃ ስለተፈፀመው ድርጊት በመንግሥትም በኮሚሽኑም ላይ ክስና ወቀሳ አሰምተዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

ሰላማዊ ሰዎችን የገደሉና ያቃጠሉ ማንነታቸው ተለይቶ ተጠያቂ እንዲሆኑ ኢሰመኮ ጠየቀ