ከትግራይ የተፈናቀሉ ቆቦ መግባታቸውን ከንቲባው ተናገሩ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ከትግራይ የተፈናቀሉ ቆቦ መግባታቸውን ከንቲባው ተናገሩ

ትግራይ ክልል ውስጥ በተከሰተው የምግብ እጥረት ምክንያት ከ200 በላይ ሰዎች ቆቦ ከተማ መግባታቸውን የከተማዋ ከንቲባ ገለፁ።

የትግራይ ክልል የውጭ ግንኙነት አስተባባሪ መሆናቸውን የሚናገሩት ካናዳ የሚገኙት አቶ ዮሃንስ አብርሃም ዛሬ ለቪኦኤ በስልክ በሰጡት ቃል “ከቤተሰብ ጋር ለመገናኘት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከመኖራቸው ውጭ ምግብ ፍለጋ እንደ ስደተኛነት ሊመደብ የሚችል የሚታወቅ እንቅስቃሴ የለም” ብለዋል።

በጦርነቱ ምክንያት ከዋጃና ጥሙጋ ተፈናቅለው ቀደም ሲል የገቡትን ጨምሮ ከሃምሣ ሺህ በላይ ቁጥር ያለው ተፈናቃይ ከተማቸው ውስጥ እንደሚገኝ የቆቦ ከተማ ከንቲባ አቶ ሰይድ አባተ ተናግረዋል። የተፈጠረውን መጨናነቅ ለማስቀረት ተፈናቃዮቹን ወደ ሌላ ቦታ ለማዘዋወር መታቀዱንም ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ቆቦ ከሚገኙት ተፈናቃዮች ወደ 12 ሺህ ለሚጠጉት ሰብዓዊ እርዳታ መደረጉንና ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ቆቦ መግባታቸውን መስማታቸውን የዓለምአቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የኮምዩኒኬሽንስ ኃላፊ አቶ ዘውዱ አያሌው ለቪኦኤ ተናግረዋል።