በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአማሮ ልዩ ወረዳና በኦሮምያ ክልል የገላና ወረዳ ነዋሪዎች የመንግሥቱ ባለሥልጣናት “ኦነግ ሸኔ” የሚላቸው፣ እራሳቸውን “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት” ብለው የሚጠሩ ታጣቂዎች ያደርሱብናል የሚሏቸው ጥቃቶች እየተባባሱ መምጣታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።
ነዋሪዎቹ “ኢሰብዓዊ” ያሏቸው ጥቃቶችና ጉዳቶች እየደረሱባቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በጉዳዩ ላይ ከመንግሥት ባለሥልጣናትም ከታጣቂዎቹም ምላሽ ለማግኘት ያደረግናቸው ጥረቶች አልተሳኩም።
Your browser doesn’t support HTML5