ትግራይ ውስጥ በመድሃኒት እጥረት ብዙ ህይወት መጥፋቱን ባለሥልጣናቱ ገለፁ

በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ውስጥ ካሉት መድኃኒቶች በከፊል

ትግራይ ክልል ውስጥ “በመድሃኒት እጥረት ምክንያት በሦስት ወራት ከ5 ሺህ 400 በላይ ሰው ሞቷል” ሲሉን ክልሉ እያስተዳደሩ ያሉት ባለሥልጣናት ገልፀዋል።

መረጃውም 40 ከመቶ ከሚሆነው የክልሉ አካባቢ የተሰበሰበ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ከዓለም አቀፍ ተቋማት በእርዳታ የተገኘውና ወደ ክልሉ በቅርብ ጊዜ የገባው መድሃኒት የሚሸንፍነው ከሚያስፈልገው ከአምስት በመቶ በታች እንደሆነና በነዳጅ እጥረት ምክንያትም ከመቀሌ ከተማ ውጭ ለሚገኙ የጤና ተቋማት ማከፋፈል አለመቻላቸውን አመልክተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ትግራይ ውስጥ በመድሃኒት እጥረት ብዙ ህይወት መጥፋቱን ባለሥልጣናቱ ገለፁ