ከኦሮምያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ተፈናቅለው በኦሮምያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን አንፊሎ ወረዳ ውስጥ መጠለላቸውን የሚናገሩ ሰዎች ላለፉት ዘጠኝ ወራት ድጋፍ አለማግኘታቸውንና ለችግር መጋለጣቸውን አስታውቀዋል። ከረሃብም የተነሳ የሞቱ ህጻናትና እናቶች አሉ ይላሉ አንዳንድ ለቪኦኤ አስተያዬታቸውን የሰጡ ተፈናቃዮች።
የወረዳው አስተዳዳሪና የቄለም ወለጋ ዞን አደጋ ስጋት አመራሮች ድጋፉ የተቋረጠው በአካባቢው በነበረው የጸጥታ ችግር መሆኑን ተናግረዋል። በረሃብ ምክንያት ግን ተከሰተ ስለተባለው ሞት መረጃ እንደሌላቸው ገልፀዋል።
የኦሮምያ ክልል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ምክትል ኮሚሽነር ገረሙ ኦሊቃ "ተፈናቃዮቹን መልሶ ለመርዳት እየተሠራ ነው " ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።