ኢትዮጵያውያን 126ኛውን የአድዋ ድል በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ ላይ አክብረዋል

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያውያን 126ኛው የአድዋ ድል በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ ላይ አክብረዋል

በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በሚኒሊክ አደባባይ ተከብሯል። የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር አባላት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት፣ በሚኒሊክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን ከተቀመጠ በኋላ ወደ አድዋ ድልድይ በማቅናት ቀሪ የበዓሉን ሥነ ስርዓት አከናውነዋል፡፡

በዓሉ በዓድዋ ድልድይ እንዲከበር መወሰኑ፣ ከቦታው ጋር በተያያዘ ቅሬታ ፈጥሮ መነጋገሪያ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዳግማዊ ሚኒሊክ አደባባይ በዓሉን ካከበሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መካከል የተወሰኑት ስለበዓሉ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን 126ኛው የአድዋ ድል በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ ላይ አክብረዋል