የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ቀጥሏል?

  • ቪኦኤ ዜና

አቶ ዋሲሁን በላይ የምጣኔ ኃብት ባለሞያ

ኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥ ባለችበት ያለፉት ስድስት ወራት ግዜ ውስጥ የኢኮኖሚ ዕድገቱ መቀጠሉን ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መናገራቸው ይታወሳል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የምጣኔ ኃብት ባለሞያዎች ምን ይላሉ? የምጣኔ ኃብት ባለሞያው አቶ ዋሲሁን በላይን ጠይቀናል። በቅርቡ ከቪኦኤ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ኃብት መምሕርና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገዳ ስለ ዋጋ ንረት የሰጡት አስተያየት የተካተተበትን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ቀጥሏል?