የአድዋ ድል በዓል ማክበሪያ ቦታ ውዝግብ እልባት አግኝቷል

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

የአድዋ ድል በዓል ማክበሪያ ቦታ ውዝግብ እልባት አግኝቷል

ከትናንት ጀምሮ መነጋገሪያ ሆኖ የቆየው የአድዋ ድል በዓል የሚከበርበት ቦታ ጉዳይ እልባት ማግኘቱ ታውቋል። በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ሌሎች የመንግሥት አካላት ቀደም ብሎ ተገልፆ የነበረውን የቦታ ለውጥ በመቃወም የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበርም፣ በትናንትናው ዕለት መግለጫ አውጥቶ የነበረ ሲሆን የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ አሁን ጉዳዩ እልባት ማግኘቱንና በተለመደው ቦታ በዳግማዊ ሚኒሊክ አደባባይ እንደሚከበር ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

የበዓል ማክበሪያ ቦታው በአዋጅ የፀደቀ መሆኑን ያስታወሱት አንድ የሕግ ባለሞያ ከአዋጅ ውጪ ቦታን መቀየር እንደማይቻል ተናግረዋል።