የወባ ወረርሽኝ ሥርጭት መጨመር በደቡብ ክልል

Your browser doesn’t support HTML5

የወባ ወረርሽኝ ሥርጭት መጨመር በደቡብ ክልል

ከዐስር ዓመታት በኋላ እንደገና በተቀሰቀሰው የወባ ወረርሽኝ ባለፉት ስድስት ወራት 24 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።

የወረርሽኙ የሥርጭት መጠንም 23 በመቶ መጨመሩን የክልሉ ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከል እና ጤና ማጎልበት ዳይሬክቶሬት ዲሬክቴር አቶ ማሌ ማቴ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በሽታው እንደ አዲስ መሰራጨት የጀመረው የኬሚካል ርጭት ባለመካሄዱ፣ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ይለገስ የነበረው የአልጋ አጎበር በመቋረጡና በመዘናጋር ምክኒያት ተገልጿል። ስርጭቱን ለመግታትም የተጓደሉ ነገሮችን ማሟላት እንደሚያስፈልግ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል።