ታይላንድ ከኮቪድ-19 ተጠቂዎች ቁጥር አሳስቧታል

ፎቶ ፋይል፦ የጤና ባለሞያዋ የኮቪድ-19 ክትባት ሊሰጡ በባንኮክ፣ ታይላንድ።

የኮቪድ-19 ከተከሰተ ወዲህ የኢኮኖሚ ሁኔታዋ እያንሰራራ የሚገኘው ታይላንድ መስቀለኛ መንገድ ቆማለች። የኢኮኖሚ ሁኔታዋ መሻሻሉን በበጎ የምታየው ሀገር በሀገሪቱ ውስጥ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር ግን አሳሳቢ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በዓለም አቀፍ ቱሪዝም ላይ የተመሰረተችው እስያዊት ሀገር፣ ዘርፉን ለማነቃቃት የተከተቡ ጎብኝዎች ተለይተው የሚቆዩበትን አሰራር አንስታለች። ከዚያ ጊዜ ወዲህ በሽዎች የሚቆጠሩ ጎብኝዎች ወደ ሀገሪቱ ገብተዋል።

በዚያው ልክ ደግሞ በኮቪድ-19 የሚያዙ ዜጎቿ ቁጥር አሻቅቧል። በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የሆነው 24ሺ ባላይ የሆነው የተያዙት ቁጥር ተመዝግቧል። ባለሙያዎች የተጋላጭነት መጠን ለመቀነስ ተጨማሪ እርምጃዎች ሊወሰዱ እንደሚገበ መክረዋል።