የአፍሪካ የጤና ባለሥልጣናት የተሻለ ቅንጅት ያለው የኮቪድ-19 ክትባቶች ሥርጭት ይረጋገጥ ዘንድ ጥሪ አቀረቡ።
ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰበት ካለፈው ሁለት ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበው ክትባት መጠን ከተጠየቀው በላይ ሆኗል። ይሁንና የማቀዝቀዣ እጥረት እና ደካማ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ከክተረባት ፍትሃዊ ሥርጭት ጋር በተያያዘ ተግዳሮት መደቀናቸውን የጤና ባለሥልጣናት ትናት በናይጄሪያ በነበረ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።
የአፍሪካ ህብረት የክትባት ማዳረስ ህብረት ያዘጋጀው ስብሰባ፣ ሀገራት የኮቪድ-19 ክትባትን ለህዝባቸው ለማዳረስ የገጠሟቸው ተግዳሮቶችን አጉልቶ ለማሳየት ያለመ ነበር።
1.2 ቢሊየን ከሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ መካከል 20 በመቶው ቢያንስ አንድ ጊዜ ክትባት አግኝቷል። ከ70 በመቶው በላይ የሆነ ህዝባቸው ከተከተበባቸው በርካታ ምዕራባዊያን ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ይቁ ቁጥር አናሳ ነው።