የቤኒሻንጉል ጉምዝ የፀጥታ ችግር ሰዉን ለተረጂነት ዳርጎታል

Your browser doesn’t support HTML5

የቤኒሻንጉል ጉምዝ የፀጥታ ችግር ሰዉን ለተረጂነት ዳርጎታል

ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ በተደጋጋሚ እየተከሰት ባለው ግጭት፣ ሁከትና አለመረጋጋት ምክንያት 62 ከመቶ የሚሆነውን የክልሉን ነዋሪ ለተረጂነት ሊያጋልጠው እንደሚችል ክልሉ አስታውቋል።

ለሰላሙ ችግር አፋጣኝ ምላሽ ካልተሰጠ ሁኔታው በአጭር ጊዜ ሊባባስና የተረጂው ቁጥር በሁለት ወራት ውስጥ ወደ አሳሳቢ ደረጃ እንደሚያድግ ተነግሯል።

አሁንም ከአራት መቶ ሺህ በላይ ሰው አፋጣኝ የምግብና ሌላም ሰብዓዊ ድጋፍ ፈላጊ መሆኑን የክልሉ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ቢሮ ኃላፊ ተካልኝ ታሲሳ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።