የዋግ ህምራ ተፈናቃዮች የበረታ የምግብና የመጠለያ ችግር እንዳለባቸው ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

የዋግ ህምራ ተፈናቃዮች የበረታ የምግብና የመጠለያ ችግር እንዳለባቸው ገለፁ

አማራ ክልል ውስጥ አሁንም በህወሃት ቁጥጥር ሥር ናቸው ከሚባሉት አካባቢዎች አንዱ ከሆነው ዋግ ኅምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የተለያዩ ወረዳና ቀበሌዎች የተፈናቀሉ ከ35 ሽህ በላይ ሰዎች በመጠለያ ጣቢዎች እንደሚገኙ ተገልጿል።

ተፈናቃዮቹ ከፍተኛ የምግብና የመጠለያ ችግር እንዳለባቸው ለአሜሪካ ድምፅ አሳውቀዋል።

የተፈናቃዩ ቁጥር በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን የሚናገረው የዞኑ አስተዳደር ፌዴራል መንግሥቱና ዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ እንዲደርሱላቸው ጠይቋል።