የሙርሌ ታጣቂዎች በደቡብ ሱዳናዊያንም ላይ ወንጀል የሚፈፅሙ መሆናቸውን የደቡብ ሱዳን የታላቁ ፒቦር አካባቢ አስተዳደር ገልጿል።
ሰላማዊ ሰዎችን የሚገድሉትና ልጆች የሚጠልፉትም ከኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ደቡብ ሱዳን ውስጥም መሆኑን የአካባቢው ቃል አቀባይ ጃይ አዲንጎራናይ አመልከተዋል።
ታጣቂዎቹ ድርጊቱን እንዲያቆሙና የተጠለፉትን ሕፃናት ለማስመለስ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር መነጋገራቸውን ገልፀው በተነጋገሩበትም ሰሞን ግድያና ጠለፋ መፈፀሙን ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5