ራሳቸውን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብለው በሚጠሩ፣ መንግሥት ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራቸውና የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የፈረጃቸው ቡድን ታጣቂዎች ከአማሮ ወረዳ ሦስት ቀበሌዎች ሦስት ሰዎች መግደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ።
ታጣቂዎቹ እያደረሱት ነው ያሉት ጥቃት መቀጠሉንና እስካሁን በውል ያልታወቁ ከብቶች መዘረፋቸውንም ተናግረዋል።
የአሜሪካ ድምፅ በስልክ ያነጋገራቸው በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና እና ሱሮ ባርጉዳ ወረዳዎች ነዋሪ የሆኑ ግለሰቦች በታጣቂዎች ምክኒያት ኑሯቸው እየተጎሳቆለ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ጥቃት እየደረሰባቸው የሚገኘውም ራሳቸውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ብለው በሚጠሩና መንግሥት ኦነግ ሸኔ እያለ በሚጠራቸው ታጣቂ ቡድኖች መሆኑን ተናግረዋል።
ጥቃቱ እየደረሰ ያለው በጌዴኦ ዞን ኮቾሬ ወረዳ 10 ቀበሌያትን ጨምሮ የአማሮ ቀበሌያት ነዋሪዎች ጭምር ላይ መሆኑን ገልፀዋል።
ራሳቸውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ብለው በሚጠሩ ፣መንግሥት ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራቸውና የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ከፈረጃቸው ቡድን ቃል አቀባይ በኩል ምላሽ ለማግኘት በስልክ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
ዝርዝር ዘገባው ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5