ድሬዳዋ —
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ /ዩኤስኤአይዲ/ በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ያጋጠሙ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ባለፈው ዓመት ብቻ 18 ቢሊዮን ብር መመደቡንና በዚህ ዓመትም የከፋ ችግር ላለባቸው ክልሎች ተጨማሪ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
የድርጅቱ ዳይሬክተር በሶማሌ ክልል በመገኘትም በድርቁ ለተጎዱ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። የኤጀንሲው ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ለሁለት ቀናት በሶማሌ ክልል የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ በሶማሌ ክልል የተመለከቱት ድርቅ አስቸኳይ ምላሽ ተናግረዋል።