የታላቁ ሩጫ አረንጓዴ ዘመቻ

Your browser doesn’t support HTML5

የታላቁ ሩጫ አረንጓዴ ዘመቻ

በአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ፌስቲቫልም እንደሆነ የሚነገርለት ታላቁ ሩጫ ለ21ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ባካሄደው ውድድር ላይ በጀመረው የአረንጓዴ ዘመቻ ከ 350 ኪሎግራም በላይ የሚመዝን ደረቅ ቆሻሻ ተሰብስቦ እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረጉን አስታውቋል። በ21 አመታት ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አረንጓዴ ዘመቻን የተቀላቀለው ታላቁ ሩጫ በቀጣይ በሀገሪቱ ላይ የሚያካሂዳቸው ውድድሮች የአካባቢ ጥበቃን ታሳቢ ያደረጉና የህብረተሰቡን ግንዛቤ የሚያሰፉ መሆናቸውንም ገልጿል። ስመኝሽ የቆየ በታላቁ ሩጫ ስለተከናወነው የአረንጓዴ ዘመቻና ጅማሮው ያመጣው ውጤት ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የኦፕሬሽን ዳይሬክተር ዳግም ተሾመ ጋር ቆይታ አድርጋለች።