የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ውሳኔዎች

Your browser doesn’t support HTML5

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ውሳኔዎች

የአፍሪካ ሕብረት 35ኛው የመሪዎች ጉባዔ በአህጉሪቱ ወቅታዊ ፈተናዎች ዙሪያ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።

አዲሱ የሕብረቱ ሊቀመንበር የሴኔጋል ፕሬዚደንት ማኪ ሳል፣ ጉባዔው መጠናቀቁን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ በተለይ የሰላም እና ጸጥታ ችግር ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች ልዩ ትኩረት እንደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

በአህጉሪቱ እየተለመደ የመጣው የመፈንቅለ መንግሥት ተግባር በምንም መልኩ ተቀባይነት እንደሌለውም በአጽንኦት አብራርተዋል፡፡

በሕብረቱ ጉባዔ ጉዳይ ለአሜሪካ ድምጽ አስተያየታቸውን የሰጡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት ትምሕርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰርና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ዮናስ አዳዬ፣ አፍሪካ ውስጣዊ ችግሮቿን በውስጣዊ መፍትሔ ካልፈታች ለዘመናት የዘለቀው የሰላምና ጸጥታ ችግር መፍትሔ እንደማያገኝ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።