የቦረና ዞንና የሶማሌ ድርቅ አሳሳቢ እየሆነ ነው

በቦረና ዞንና በሶማሌ የደረሰው ድርቅ

በኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን ውስጥ መስከረም ውስጥ የተጠበቀው ዝናብ ባለመጣሉና ለስድስት ተከታታይ ወራት እርጥበት በመጥፋቱ ምክንያት የተከሰተው ድርቅ ቁጥራቸው የበዛ ከብቶችን መጨረሱን የክልሉ ግብርና ፅህፈት ቤት የእንስሣት ኃብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።

በኦሮምያ ክልል የግብርና ፅህፈት ቤት የእንስሣት ኃብት ልማት ቢሮ አስተባባሪ ዶክተር ቃሲም ጉዮ እስካሁን ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ከብቶች መሞታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና የኦሮምያ ፕሬዚዳንት አቶ ሺመልስ አብዲሳ ዛሬ ቦረና ተገኝተው የድርቁን ሁኔታና ያስከተለውን ጉዳይ ተመልክተዋል።

(ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።)

Your browser doesn’t support HTML5

የቦረና ዞንና የሶማሌ ድርቅ አሳሳቢ እየሆነ ነው