የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል ሥራ እንዲፋጠን የአፍሪካሚኒስትሮች ወሰኑ

Your browser doesn’t support HTML5

የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል ሥራ እንዲፋጠን የአፍሪካ ሚኒስትሮች ወሰኑ

የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት በዛሬው የሁለተኛ ቀን ውሎው የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ስለመቆጣጠርና በሌሎችም አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በዝግ ተወያይቷል። ምክር ቤቱ አዲስ አበባ ውስጥ እየተገነባ የሚገኘው የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠርያና መከላከያ ማዕከል በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ መወሰኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀመኮንን ከቱኒዚያ እና ከሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ከጉባዔው ጎን ለጎን በተናጠል መወያየታቸውንና ከአባይ ውኃ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ሃገሮቹና የአረብ ሊግ ያራምዷቸዋል ያሏቸውን አቋም እንዲመረምሩና እንዲያስተካክሉ መጠየቃቸውንም ቃል አቀባዩ አመልክተዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪድዮ ዘገባ ያገኛሉ።)