የአፍሪካ ኅብረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አርባኛ ጉባዔ ተጀመረ

Your browser doesn’t support HTML5

የአፍሪካ ኅብረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አርባኛ ጉባዔ ተጀመረ

የአፍሪካ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክር ቤት አርባኛ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀምሯል።

በሚኒስትሮቹ ጉባዔ መክፈቻ ላይ የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ በኮቪድ-19 ጫና፣ በአፍሪካ-2063 አጀንዳና በሌሎችም አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ማብራርያ ሰጥተዋል።

ጉባዔውን እየተከታተለ ያለው ገልሞ ዳዊት ተጨማሪ አለው።

ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ከ25 ደቂቃ በላይ በዘለቀው የጉባዔው መክፈቻ ንግግራቸው በተለይ ለአፍሪካ የፀጥታና ደኅንነት ችግር ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ በአፅንዖት አሳስበዋል።