ጥምቀት በደሴ

Your browser doesn’t support HTML5

ጥምቀት በደሴ

ጥምቀት ድምቀት በሆነባት ደሴ በሽዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን አደባባይ ወጥተው “ከዓመት ቆጥሮ ዓመት ላሻገራቸው ፈጣሪያቸው ምስጋና አቅርበዋል።”

የዕድሜ፤ የፆታና፣ ማኅበራዊ ደረጃ ልዩነት የሌለበት አብሮነት የተንፀባረቀበት ጥምቀት ከቆቦ እሰከ ወልዲያ ከመርሳ እስከ ውጫሌ፣ ከኃይቅ እስከ ደሴ፣ ከኮምቦልቻ እስከ ከሚሴ፣ ከሸዋ ሮቢ እስከ ደብረ ሲና በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል።

ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እንደየአካባቢው ልዩነት ከቀናት እስከ ወራት ወታደራዊ ግጭት ተስተናግዶባቸው የነበረ ከመሆኑ አንፃር በዓሉ በሰላም መከበሩ የተለየ ድባብና ትርጉም ሰጥቶታል።