አማራ መጠለያ ጣቢያዎችን እየዘጋ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

አማራ መጠለያ ጣቢያዎችን እየዘጋ ነው

የአማራ ክልል መንግሥት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ከፍቷቸው የነበሩ መጠለያ ጣቢያዎችን እየዘጋ መሆኑን አስታውቋል።

እስካሁን ወደ አራት መቶ ሺህ የሚጠጋ ቁጥር ያላቸው ተፈናቃዮች ወደየቀያቸው መመለሳቸውን የክልሉ የአደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ኮሚሽን ዛሬ ገልጿል።