ለዘላቂ ሰላም መፍትኄ

Your browser doesn’t support HTML5

ለዘላቂ ሰላም መፍትኄ

“አማፅያኑ የትግራይ ተዋጊዎች ይዘዋቸው ከነበሩት የአማራና የአፋር ከተሞች መልቀቃቸው ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ዋና ከተማዪቱ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ሊደርስ ይችላል በሚል ሲያሳዩ የነበረውን ስጋት ቢያስወግድም ጦርነቱ አሁንም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ዋጋ እያስከፈለ ነው” ሲሉ ክራይስስ ግሩፕ የሚባለው የቀውስ አጥኚና ተንታኝ ተቋም የአፍሪካ ቀንድ ቅርንጫፍ ኃላፊ ሙሪቲ ሙቲጋ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

“የኢትዮጵያ ችግር በፖለቲካዊ ውይይት ካልተፈታ ግጭቱ ሥር ሰድዶ ሃገሪቱን የማትወጣው ችግር ውስጥ ሊከታት ይችላል” ሲሉም ስጋታቸውን ገልፀዋል።