አዲስ አበባ —
የህወሓት ኃይሎች ወደ አማራ ክልል ዘልቀው መግባታቸውን ተከትሎ ከ400 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍል ተፈናቅሎ፣ ወደ ሰሜን ሸዋ መምጣቱን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ገለጸ፡፡
ለተፈናቃዮቹ የእለት ምግብ እርዳታ ለማድረስ ጥረቶች ቢደረጉም የቁጥራቸው በየጊዜው መጨመር ተጽእኖ ማሳደሩን ጽ/ቤቱ ጠቅሷል፡፡
ተፈናቃዮቹ በበኩላቸው የህወሓት ኃይሎች በተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ከፍተኛ የኑሮ ውድነት መከሰቱን በማውሳት ጥለዋቸው የመጡት ቤተሰቦቻቸው ጉዳይ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5