በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ታጣቂዎችን እንደሚዋጋ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ታጣቂዎችን እንደሚዋጋ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የፓርቲው አመራር፣ አባላትና ደጋፊዎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሚገኙ "የህወሓት ተካላኪ ጸረ-ሰላም ኃይሎች" ናቸው የተባሉትን በግንባር ለመዋጋት ዝግጅት እንዲያደርጉ መወሰኑን አስታወቀ።

የፓርቲው ፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ተሰማ ከመንግሥት ጋር ልዩነት ቢኖራቸውም በዚህ ዘመቻ ለሃገር ህልውና አብረው መቆማቸውን ነው ለቪኦኤ የተናገሩት።

የክልሉ መንግሥት "የቦዴፓ ውሳኔ የሚበረታታ ነው" ሲል አስታውቋል።