በኢትዮጵያ ጉዳይ የአምባሳደር ፌልት ማን ተስፋና ስጋት

የአምባሳደር ፌልት ማን

የአምባሳደር ፌልት ማን

የህወሃት አማፂያን ወደ አዲስ አበባ ለመግባትም ሆነ የጂቡቲን መሥመር ለመያዝ የሚያደርጉትን ጥረት አጥብቀው እንደሚቃወሙ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ አገራቸው የተመለሱት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፈሪ ፌልትማን አስታውቀዋል።

ፌልትማን ኢትዮጵያ ውስጥ የነበራቸውን የሁለት ቀናት ቆይታ አስመልክቶ ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በመንግሥትና በህወሃት መካከል ውይይት መጀመር የሚያስችል ጭላንጭል ማየታቸውን የጠቆሙ ቢሆንም ከዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ይልቅ የጦርነቱ መጋጋል እያየለ መሄድ ግን ሥጋት እንደፈጠረባቸው አስታውቀዋል።

/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ ጉዳይ የአምባሳደር ፌልት ማን ተስፋና ስጋት