ኦባሳንጆ ወደ መቀሌ የተጓዙት እውነትን ለማፈላለግ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ

  • እስክንድር ፍሬው

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒሰትር ዲኤታ ሠላማዊት ካሣ

የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛና የቀድሞው የናይጀሪያ ኘሬዚዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ወደ መቀሌ ተጉዘው ከህወሃት መሪዎች ጋር መወያየታቸውን ኅብረቱ አስታውቋል ።

ልዩ ልዑኩ ከህወሃት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ጋር ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ጌታቸዉ ረዳ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥትም በበኩሉ ኦባሳንጆ ወደ መቀሌ መጓዛቸውን አረጋግጧል።

ጉዟቸውም እውነትን የማፈላለግና መረጃዎችን ከሁሉም አካል የመሰብሰብ ተልእኮ መሆኑን የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒሰትር ዲኤታ ሠላማዊት ካሣ ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል።

"በመንግሥት በኩል የሚደበቅ ምንም ነገር የለም" ያሉት ሚኒስትር ዲኤታዋ፤ ማናገር አለብኝ ብለው የሚያስቧቸውን አካላት እንዲያናግሩ ሁኔታው መመቻቸቱን ገልፀዋል።